የዓለም እንስሳት ቀን በኢትዮጵያ

መስከረም 29/2014 (ዋልታ) ደንና ህይወት ለሰው፣ ለእንስሳትና ለምድር ዘላቂነት በሚል መሪ ቃል በዓለም ለ91ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ7ኛ ጊዜ የዓለም የእንስሳት ቀን እየተከበረ ነው።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ባዘጋጀው መድረክ የዱርና የቤት እንስሳት ለተፈጥሮ እና ለሰው ልጅ የሚያበረክቱትን በጎ አበርክቶ በማውሳት ስለ እንስሳት ጤናና መብት ግንዛቤ የሚፈጥሩ መልዕክቶች ተላልፈዋል።