የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በትራንስፖርት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት፣ የላዳ ታክሲ ማህበራት እና ተራ አስከባሪዎች ትብብር በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የታደሱ የአቅመ ደካሞችን ቤት አስረከቡ፡፡ በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በከተማ አስተዳደሩ እና በሌሎች አካላት ትብብር ከ2ሺ በላይ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ታድሰው ለባለቤቶቹ መሰጠታቸውን ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡